ወሮታ ለፍትሕ የአል-ሸባብ ቁልፍ መሪ ስለሆነው ሀሰን አፍጉዬ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ አፍጉዬ ከሃሰተኛ የበጎ አድራጎት ሥራ እስከ ገንዘብ ማስባሰብ እንዲሁም ማስጨመርበር እና እገታ የመሳሰሉ ተግባራት የሚፈጸሙበት ውስብሰብ የፋይናንስ ኔትወርክ ይመራል፤ ይህንንም በዩናይትድ ስቴትስ ሽብርተኛ የተባለውን አል-ሸባብ ለመደገፍ ይጠቀምበታል፡፡ አፍጉዬ ለቡድኑ ሥራዎች መቀጠል ወሳን ነው ተብሎ ይታሰባል፡፡