ሁራስ አል-ዲን (ኤችኤዲ) ከአል-ቃዒዳ ጋር ግንኙነት ያለው የጂሃድ ቡድን ሲሆን፣ የተመሠረተውም በሶሪያ በ2010 ዓ.ም. መጀመሪያ በርካታ ቡድኖች ከሃያት ታህሪረ አል-ሻም (ኤችቲኤስ) ተገንጥለው ከወጡ በኋላ ነበር፡፡
በጳጉሜን 05 ቀን 2011 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሁራስ አል-ዲን (ኤችኤዲ)ን ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የሁራስ አል-ዲን ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከሁራስ አል-ዲን ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡