ወሮታ ለፍትሕ ስለ ሀፊዝ አብዱል ራህማን ማኪ በሌላ ስሙ አብዱልራህማን ማኪ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $2 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ ማኪ በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጀት (ኤፍቲኦ) ተብሎ በተሰየመው ላሽ ካር -ኢ-ጣዪባ (ኤልኢቲ) ውስጥ በልዩ ልዩ የአመራር ቦታዎች ሰርቷል፡፡ ለኤልኢቲ ኦፕሬሽኖች ገንዘብ አሰባስቧል፡፡
በ2012 ዓ.ም. የፓኪስታን የፀረ ሽብር ምክር ቤት ማኪን ለሽብርተኝነት ገንዘብ በማቅረብ ጥፋተኛ አድርጎት እስር ፈርዶበታል፡፡ የፓኪስታን የፍርድ ስርዓት የኤልኢቲ መሪዎችን እና ጀሌዎች ቀደም ሲል ከእስር በመፍታቱ ዩናይትድ ስቴትስ አሁንም ስለ ማኪ መረጃ ትፈልጋለች፡፡
በጥቅምት 25 ቀን 2003 ዓ.ም.፣ የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስቴር ማኪ ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት ሌሎች እርምጃዎች እንደተጠበቁ ሆነው በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የማኪን ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከማኪ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው ኤልኢቲ ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡