ወሮታ ለፍትሕ ስለ ሀፊዝ ሳዒድ፣ በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት (ኤፍቲኦ) ተብሎ የተመዘገበው የላሽካር – ኢ – ጣይባ (ኤልኢቲ) መስራች እና መሪ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $10 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ ሳዒድ በኅዳር 2000 ዓ.ም. በሙምባይ፣ ህንድ የተፈፀመውን 4 ቀናት የፈጀ የሽብርተኛ ጥቃት በማቀድ ውስጥ ተሳትፏል፤ በዚህ ጥቃት 6 አሜሪካውያንን ጨምሮ 166 ግለሰቦች ሞተዋል፡፡
በ2012 ዓ.ም. የፓኪስታን የፀረ ሽብር ምክር ቤት ማኪን ለሽብርተኝነት ገንዘብ በማቅረብ ጥፋተኛ አድርጎት እስር ፈርዶበታል፡፡ የፓኪስታን የፍርድ ስርዓት የኤልኢቲ መሪዎችን እና ጀሌዎች ቀደም ሲል ከእስር በመፍታቱ ዩናይትድ ስቴትስ አሁንም ስለ ማኪ መረጃ ትፈልጋለች፡፡
ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት ሌሎች እርምጃዎች እንደተጠበቁ ሆነው በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የሳዒድን ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከሳዒድ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው ኤልኢቲ ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡ በታኅሳስ 01 ቀን 2001 ዓ.ም. ሳዒድ በተባበሩት መንግስታት 1267/1989 የአል-ቃዒዳ ማዕቀብ ኮሚቴ ከአል-ቃዒዳ ሽብርተኛ ድርጅት ጋር ግንኙነት እንዳለው ግለሰብ በዝርዝር ውስጥ ተካቷል፤ ስለሆነም አለም አቀፍ ማዕቀብ ተጥሎበታል፡፡