ለወሮታ ለፍትሕ የማኅበረሰባችን አካል ለመሆን ፈቃደኛ በመሆንዎ እናመሰግናለን፡፡ የግል መረጃዎችዎ እንዲጠበቁ እና ለግላዊነት ላለዎት መብት ግዴታ ገብተናል፡፡
ይህ የግላዊ መረጃ ማሳወቂያ ከዚህ በሚከተሉት ሁኔታዎች የእርስዎን ግላዊ መረጃዎች በምን መልኩ ጠቅም ላይ አንደምናውል ያብረራል፡-
በዚህ የግላዊ መረጃዎች ማሳወቂያ ውስጥ
የዚህ የግልዊ መረጃዎች ማሳወቂያ ዓላማ የትኞቹን መረጃዎች እንደምንሰብሰብ፣ እንዴት እንደምንጠቀምባቸው እና ከእነርሱ ጋር በተያያዘ የእርስዎ መብቶች ምን እንደሆኑ በተቻለን ሁሉ በግልጽ ማብራራት ነው፡፡ በዚህ የግላዊ መረጃ ማሳወቂያ እርስዎ የማይስማሙበት ማንኛውም ሁኔታ ካለ፣ እባክዎን የእኛን አገልግሎት መጠቀምዎን ወዲያውኑ ያቁሙ፡፡
እባክዎን ይህንን የግላዊ መረጃ ማሳወቂያ በጥንቃቄ ያንብቡ፤ ምክንያቱም የምንሰበስባቸውን መረጃዎች እንዴት እንደምናስተናግድ ለመረዳት ያስችልዎታል፡፡
በአጭሩ፡- የእኛን ድረ ገጽ በሚጎበኙበት ጊዜ አንዳንድ መረጃዎችዎ ለምሳሌ የኢንተርኔት ፕሮቶኮል አድራሻ እና/ወይም ብራውዘር እና የሚጠቀሙበት መሣሪያ ባሕርያት መረጃዎች በአውቶማቲክ ዘዴ ይሰበሰባሉ፡፡
ድረገጹን በሚጎበኙ፣ በሚጠቀሙ ወይም በሚያዩ ጊዜ ጊዜ አንዳንድ መረጃዎች በአውቶማቲክ ዘዴ ይሰበሰባሉ፡፡ ይህ መረጃ የእርስዎን ማንነት (ለምሳሌ ስምዎን ወይም ዝርዝር መረጃዎትን) ለይቶ አያስቀምጥም፤ ነገር ግን የሚጠቀሙበትን መሣሪያ (ዲቫይስ) እና የአጠቃቀም መረጃ፣ ለምሳሌ አይፒ አድራሻዎን፣ የብራውዘር እና የመገልገያዎን ባሕርያት፣ ኦፕሬቲንግ ሲስተም፣ የቋንቋ ምርጫዎች፣ የሚያጣቅሰውን ዩአርኤል፣ የመገልገያዎን ስም ፣ አገር፣ የሚገኙበትን ስፍራ የእኛን ድረ ገጽ የተጠቀሙበትን ሁኔታ እና ሌሎች ቴክኒካዊ መረጃዎችን ሊይዝ ይችላል፡፡ የእኛን ድረገጽ ደህንነት እና አሰራር ለመጠበቅ እንደሁም ለውስጣዊ ትንተና እና ሪፖርት ለማቅረብ እንዲረዳ በዋናነት ይህ መረጃ ይፈለጋል፡፡
እንደ በርካታ ሥራዎች ሁሉ፣ በኩኪዎች እና በተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎች አማካኝነትም መረጃዎች እንሰበስባለን፡፡
የምንሰበስባቸው መረጃዎቸ ከዚህ የሚከተሉትን ያካትታሉ፡-
በዌብሳይታችን አማካኝነት የሰበሰብናቸውን መረጃዎች ከዚህ በማስከተል ለተዘረዘሩት ልዩ ልዩ የቢዝነስ ዓላማዎች ጥቅም ላይ እናውላቸዋለን፡-
በአጭሩ፡- ኩኪዎችን እና ሌሎች ተመሳሳይ መከታተያ ቴክኖሎጂዎችን (እንደ ቢኮንስ እና ፒክስልስ ያሉትን) መረጃ ለመሰብሰብ ወይም ለማስቀመጥ ልንጠቀም እንችላለን፡፡
ኩኪዎች እና ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎች ወደ ዌብሳይታችን ሲመለሱ በአውቶማቲክ ዘዴ የእርስዎን ማንነት ለማወቅ ያስችለናል፡፡ ኩኪዎች የድረገጽ ትራፊክ እንቅስቃሴን ለማየት፣ ድረገጹን ለማሻሻል እና የትኞቹ አገልግሎቶች ከሌሎቹ ይልቅ ምን ያህል ታዋቂ መሆናቸውን ለመለየት እንድንችል ይረዱናል፡፡ እንዲሁም የተጠቃሚዎች ባሕርይ የሚፈልጓቸውን ነገሮች ለመለየት ስለሚያስችሉ፣ በእነዚያ ጉዳዮች ላይ ከስተማይዝድ ኮንቴንት እና ማስታወቂያ ለማቅረብ እንችላለን፡፡
አብዛኞቹ የዌብ ብራውዘሮች ከአሰራራቸው ጀምሮ ኩኪዎች እንዲቀበሉ ተደርገው የተሰሩ ናቸው፡፡ ብራውዘርዎ ኩኪዎችን እንዲያስወግድ ሊደርጉት ይችላሉ፤ ይህም አንዳንድ የድረ ገጻችን ገጽታዎች ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል፡፡
በአጭሩ፡- በአደረጃጀት እና በቴክኒክ የደህንነት አጠባበቅ ዘዴዎች የግል መረጃዎችዎን ለመጠበቅ እንፈልጋለን፡፡
የምናካሂዳቸውን የማናቸውንም የግል መረጃዎች ለመጠበቅ አግባብነት ያላቸውን የቴክኒክ እና የድርጅት ደህንነት እርምጃዎች እንወስዳለን፡፡ ሆኖም ግን፣ ደህንነት መጠበቂያዎች ቢኖሩን እና ጥረቶች ብናደርግም እንኳን፣ በኢንተርኔት ወይም በመረጃ ማስቀመጥ ቴክኒሎጂ አማካኝነት የምናደርገው የማስተላለፍ ሂደት 100% ደህንነቱ የተጠበቀ ሊሆን አይችልም፤ ስለሆነም ሃከሮች፣ የሳይበር ወንጀል ፈጻሚዎች ወይም ሌሎች ፈቃድ የሌላቸው ሦስተኛ ወገኖች የእኛን የደህንነት እርጃዎች ለመስበር እና የእርስዎን መረጃዎች አግባብነት በሌለው ሁኔታ ለመሰብሰብ ፣ ለማግኘት፣ ለመስረቅ ወይም ለመለወጥ አይችሉም አንልም፡፡ እኛ የሚቻለንን ጥረት ሁሉ ብናደርግም እንኳን የግል መረጃዎችዎን ወደ እኛ ደረ ገጽ ማስተላለፍዎ ወይም ከእኛ ድር አምባ ወደ ሌላ ስለመላክዎ ኃላፊነት የሚወስዱት እርስዎ ነዎት፡፡ የእኛን ድርአምባ መጠቀም ያለብዎት ደህንነቱ በተጠበቀ ስፍራ ብቻ ነው፡፡
አብዛኞቹ የድረ ገጽ ዌብሳይቶች እና አንዳንድ የሞባይል ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች እና ሞባይል አፕሊኬሽኖች ዱ-ኖት-ትራክ (“ዲኤንቲ”)የሚል ገጽታ ወይመ ሴቲንግ ይኖቸዋል፤ እርስዎም ይህንን በመጠቀም የብራውዚንግ ተግባራትዎ ላይ ክትትል እንዳይደረግበት ወይም እንዳይሰበሰብ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ በዚህ አሁን ባለንበት ጊዜ ወጥነት ያለው ለዲኤንቲ አመላካቾች እውቅና ለመስጠት እና ተግባራዊ ለማድረግ ተፈጻሚነት ያለው ስታንዳደርድ አልተጠናቀቀም፡፡ ስለሆነም፣ በአሁኑ ጊዜ ኦንላይን ሳሉ ክትትል እንዳይደረግ (ትራክ እንዳይደረጉ) የሚጠይቁ የዲኤንቲ ብራውዘር አመላካቾች ወይም ማናቸውም ሌሎች ዘዴዎች ምላሽ አንሰጥም፡፡ ወደፊት እኛ ልንከተለው የሚገባ ስታንዳርድ ኦንላይን መከታተያ ዘዴ ተፈጻሚ ከተደረገ፣ በዚህ የግላዊ መረጃ አያያዝ ማሳወቂያ ላይ ክለሳ በማድረግ እናሳውቅዎታለን፡፡
አገልግሎቶቻችን ቁጥጥር የሚደረግባቸው እና ኦፕሬት የሚደረጉት ከዚህ ከዩናይትድ ስቴትስ ነው፤ ድረ ገጹም የተዘጋጀው ለዩናይትድ ስቴትስ ነዋሪዎች ሲባል ነው፤ ስለሆነም በዚህ ድርአምባ ላይ ከዩናይትድ ስቴትስ ወጪ የሌሎች የማናቸውም መንግሥት፣ አገር ወይም ግዛት ሕግጋት ተፈጻሚነት የላቸውም፡፡ አገልግሎቶችን በመጠቀም የሚሰጧቸው ማናቸውም መረጃዎች በዩናይትድ ስቴትስ እና በሌሎች አገራት መካከል የሚቀመጡ፣ የሚካሄዱ እና የሚተላለፉ ሲሆኑ፣ ሌሎቹ አገራት ግን እርስዎ ነዋሪ እንደሆኑበት አገር ተመሳሳይ የግል መረጃዎች ጥበቃ ላያደርጉ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን የእርስዎ የግል መረጃዎች ከአገርዎ እንዳይወጡ የሚፈልጉ ከሆነ፣ እነዚህን መረጃዎችን ለወሮታ ለፍትሕ አይስጡ፤ የእኛንም ድርአምባ አይጠቀሙ፡፡
ወሮታ ለፍትሕ ወይም የእርሱ አገልግሎት ሰጪዎች የእርስዎን የግል መረጃዎች ከአውሮፓ የኢኮኖሚ (ኢኢኤ) አካባቢ ወደ ሌሎች አገራት ሊያስተላለፍ ይችላል፤ በኢኢኤ ደረጃዎችም መሠረት እነዚህ አገራት በቂ የመረጃ ጥበቃ እንዳላቸው አልተወሰነም፡፡ የኢኢኤን ስታንዳርዶች የሚያሟሉ የመረጃ ጥበቃ እንዲደረግ ወደማይጠይቁ አገራት መረጃዎች ሲተላለፉ፣ ወሮታ ለፍትሕ ልዩ ልዩ የሕግ ዘዴዎችን በጠቀም የእርስዎን ግላዊ መረጃዎች ለመጠበቅ ይጥራል፤ ከእነርሱም መካከል አገልግሎት ሰጪዎች የውል ድንጋጌዎች እንዲያካትቱ እና የጽሑፍ ማረጋገጫ እንዲሰጡ መጠይቅ ይካተታሉ፡፡
የእርስዎን ግላዊ መረጃዎች የሚቀመጡበት ወይም የሚገኙበት ስፍራ የትኛውም ቢሆን በዚህ የግል መረጃዎች ጥበቃ ፖሊሲ መሠረት የግል መረጃዎችዎን እንይዛን፡፡
ከዩናይትድ ስቴትስ ፌዴራል መንግሥት ውጪ ካሉ ድርአምባዎች ጋር ያሉ ግንኙነቶች ወይም በወሮታ ለፍትሕ ድርአምባ ላይ የንግድ፣ የድርጅት ወይም የኮርፖሬሽን ስሞች መጠቀም ለተጠቃሚው እንደተመቸው ነው፡፡ ስለሆነም እንዲህ ያለው የስም አጠቃቀም መኖሩ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ወይም የወሮታ ለፍትሕ ፕሮግራም ማንኛውም የግሉን ዘርፍ ድርአምባ፣ ምርት ወይም አገልግሎት አጽድቋል ማለት አይደለም፡፡
በዚህ ድርአምባ ላይ የሚገኙ መረጃዎችን ፈቃድ ሳይሰጥ አፕሎድ ለማድረግ መሞከር እና/ወይም መረጃውን መለወጥ በጥብቅ የተከለከለ ሲሆን፣ በ1978 ዓ.ም. በወጣው ሕግ 18 U.S.C. § 1030 በክፍል 1001፣ ርዕስ 18 ስር በሕግ ያስጠይቃል፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን የግል መረጃዎች አያያዝ ፖሊሲን በ https://www.state.gov/privacy-policy/ ሊያገኙ ይችላሉ፡፡
ስለ ግላዊ መረጃ አያያዛችን ወይም የእርስዎን መረጃ ስለምንጠቀምበት ሁኔታ ማንኛውም ጥያቄ ካለዎ፣ የእርስዎን ግብረ መልስ በደስታ እንቀበላለን፡፡ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤታችን የግል መረጃዎች አያያዝ ደንብ ማቴሪያሎች በግላዊ መረጃ ተጽዕኖ ምዘና (ፒአይኤ) እና ሲስተምስ ኦፍ ሪከርድስ ኖቲስስ (ኤስኦአርኤን) ይገኛሉ፡፡ ስለ ግላዊ መረጃዎች አያያዝ ፖሊሲያችን ተጨማሪ መረጃ ካስፈለገዎ በ privacy@state.gov ሊያገኙን ወይም ከዚህ በሚከተለው አድራሻ ፖስታ ሊልኩልን ይችላሉ፡-
Office of Global Information Services
Privacy Office – A/GIS/PRV
State Annex 9
U.S. Department of State
Washington, DC 20006
You may choose from multiple platforms and contact us in numerous languages. To process your information efficiently, we ask you to state your information as succinctly as possible, provide your name, location, and preferred language, and upload all relevant files such as photographs, videos, and documents to support your information. An RFJ representative will soon contact you. Please be patient, as RFJ reads every tip we receive.
መረጃ ለማቅረብ እባክዎን ሲግናል ማመልከቻዎን ይክፈቱለ፡፡
ቁጥሩ የሚከተለው ነው፡- +1 202 702 7843
መረጃ ለማቅረብ እባክዎን የቴሌግራም አፕሊኬሽንዎን ይክፈቱ፡፡
ቁጥሩ የሚከተለው ነው፡- +1 202 702 7843
እባክዎን በቶር ላይ የተመሠረተ የመጃዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቻናላችንን በዚህ ያግኙ፡- he5dybnt7sr6cm32xt77pazmtm65flqy6irivtflruqfc5ep7eiodiad.onion