ስለ ተቋሙ
ስለ ተቋሙ
የዩናይትድ ስቴትስ የብሔራዊ ወሮታ ፕሮግራም የሆነው ወሮታ ለፍትሕ ዓለም ዓቀፍ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ሲባል በ1976 ዓ.ም. በወጣው ሕግ፣ የሕዝብ ሕግ 98-533 (በ22 U.S.C. § 2708 ሕግ ሆኖ በወጣው) መሠረት የተቋቋመ ነው፡፡ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዲፕሎማሲ ደህንነት ቢሮ የሚተዳደረው ወሮታ ለፍትሕ ተልዕኮው የአሜሪካዊያንን ሕይወት እና የዩናይትድ ስቴትስን ብሔራዊ ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችል መረጃ ለማግኘት ወሮታ መክፈል ነው፡፡
ከ1976 ዓ.ም. ጀምሮ ኮንግረስ ለወሮታ ለፍትሕ በሕግ የተሰጠውን ሥልጣን በአራት ሰፋፊ ምድቦች አስፍቷል፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የወሮታ ክፍያን ካጸደቀ በኋላ፣ ወሮታ ለፍትሕ ይህንኑ ያስተዋውቃል እንዲሁም ማኅበራዊ ሚዲያን፣ የማኅበራዊ ውይይት/ቻት መተግበሪያዎችን እና የተለመዱትን ሚዲያዎች ጨምሮ በሌሎችም ዘዴዎች በመጠቀም ከተደራሾች ጋር የሃሳብ ልውውጥ ያደርግበታል፡፡
የወሮታ ለፍትሕ ማስታወቂያዎች መረጃ ሰጪዎች እንደ ሲግናል፣ ቴሌግራም እና ዋትስአፕ ያሉ በርካታ ምስጢራዊ የመልክት መላኪያ አፕሊኬሽኖችን በመጠቀም በቋንቋ በተለዩት የመረጃ መስጫ መስመሮች እንዲልኩ መመሪያ አውጥቷል፡፡ እንዲሁም ግለሰቦች በኢሜል ወይም በማኅበራዊ ሚዲያ ሒሳቦች አማካኝነት መልዕክቶታቸውን ማቅረብ ይችላሉ፡፡ ወሮታ ለፍትሕ አግባብነት ያላቸውን መረጃዎች ለሌሎች የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ኤጀንሲዎች ያሳውቃል፡፡
በአንድ መረጃ ሰጪ የተሰጡ መረጃዎች አዎንታዊ ውጤት ያላመጣ እንደሆነ፣ የዩናይትድ ስቴትስ የምርመራ ኤጀንሲ እንደ ጉዳዩ ሁኔታ መረጃ ሰጪውን ለወሮታ ክፍያ ሊያጭ ይችላል፡፡ ለክፍያ እጩነት ከተለያዩ ኤጀንሲዎች በተውጣጣ ኮሚቴ ከታየ በኋላ ክፍያ መፈጸም ያለበት ስለመሆኑ ውሳኔ እንዲሰጥበት ለሚኒስትሩ ይቀርባል፡፡
በ1976 ዓ.ም. ከተጀመረ ጀምሮ ይህ ፕሮግራም በዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ ደህንነት ላይ ለተጋረጠ አደጋ መፍትሔ ለማግኘት ያገዙ፣ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችሉ መረጃዎች ለሰጡ በዓለም ዙሪያ ከ125 ሰዎች በላይ ለሚሆኑ ሰዎች $250 ሚሊዮን በላይ ገንዘብ ከፍሏል፡፡
You may choose from multiple platforms and contact us in numerous languages. To process your information efficiently, we ask you to state your information as succinctly as possible, provide your name, location, and preferred language, and upload all relevant files such as photographs, videos, and documents to support your information. An RFJ representative will soon contact you. Please be patient, as RFJ reads every tip we receive.
መረጃ ለማቅረብ እባክዎን ሲግናል ማመልከቻዎን ይክፈቱለ፡፡
ቁጥሩ የሚከተለው ነው፡- +1 202 702 7843
መረጃ ለማቅረብ እባክዎን የቴሌግራም አፕሊኬሽንዎን ይክፈቱ፡፡
ቁጥሩ የሚከተለው ነው፡- +1 202 702 7843
እባክዎን በቶር ላይ የተመሠረተ የመጃዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቻናላችንን በዚህ ያግኙ፡- he5dybnt7sr6cm32xt77pazmtm65flqy6irivtflruqfc5ep7eiodiad.onion